ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት የተመጣጠነ የውጤት ካርድ (BSC) የእቅድ ትውውቅ

የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ከመስከረም 20-21/2017 ዓ.ም ለመሪዎች በተመጣጠነ የውጤት ካርድ (BSC) እቅድ ከዋናው መስርያ ቤት ፣ ከኮቦልቻ ዋና ማስተባበርያ ጽ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ማስተባበርያ ጽ/ቤት ለሚሰሩ አሰሪዎች ኦረንቴሽን እና ገለፃ አድርጓል ።
ውይይቱ በ2017 በጀት አመት የኮርፖሬሽኑን ግቦች እና ኢላማዎችን የሚሳኩበትና ውጤቱን ለመለካት በሚያስችሉ መለኪያዎች ዙርያ ያተኮረ ነበር፡፡ ይህም ከአራቱ እይታዎች አኳያ ኢላማዎችንና መለኪያዎችን በመቅረጽ ከተገኙ ውጤቶች ጋር በማገናኘት የውስኮን አፈፃፀም ደረጃ ማዎቅ እንደሚያስችል ተገንዝበው ሁሉም ክፍሎች እና ቡድኖች ለጋራ ድርጅታዊ ግቦች መሳካት መስራት እንደሚገባቸው ግንዛቤ እንዲይዙ ተደርጓል ። በአጠቃላይ በኮርፖሬሽኑ በውጤት ተኮር እቅድ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በውይይቱ ወቅት ትኩረት የተደረገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

  • በኮርፖሬሽኑኢላማዎች፣ የአፈጻጸም መለኪያዎች ፡ በእድገት እና በአሰራር ብቃት ላይ

  • በስራ ባህልን ማሻሻል እና አመላካቾች

  • በሃብት አስተዳደር

  • በስራ በአመራር ባህሪያት ዙርያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል

  • በዘርፎች መካከል ትብብርን ለማጎልበት የሚያግዙ ነጥቦች

  • የውስኮ ግቦችን እንዴት ማሳካት እንደሚቻል

  •  የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንዴት መፍታት እንችላለን። በሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡

     

Scroll to Top