የ2017 በጀት ዓመት የመጀመርያውን ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሂደ፡፡

በ25/02/2017 የኮርፖሬሽኑን የሩብ ዓመት የዋና ዋና ተግባራት የዕቅድ አፈጻጸም  ግምገማ አካሂዷል

  1. ፊዚካል አፈፃፀም

በኮርፖሽኑ በኮንስትራክሽን ዘርፍ 5 ነባር ሜጋ ፕሮጀክቶች ፣ 30 ነባር አንስተኛ ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ፕሮጀክቶች ግንባታ በማከናወን በ2016 በጀት አመት መጨረሻ ከደረሰበት በሩብ ዓመቱ በ4.22% ለማሳደግ ታቅዶ በ2.001% ማሳደግ ተችሏል፡፡ ከሩብ ዓመቱ እቅድ አንፃር ሲታይ 47.41%  መሆኑ ተገምግሟል፤ እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና የውሃ መጠን ፍተሻ ዘርፍም 18 ጥልቅና መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ 2,567.4 ሜትር ጥልቀት፣12 የውኃ መጠን ፍተሻና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ፣ 2 የአናት ስራና የእጅ ፓምፕ ተከላ ፣ 9 የጉድጓድ ጠረጋ በጠቅላላው 41 ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማጠናቀቅ ታቅዶ 10 ጉድጓድ በ2,567.4 ሜትር ጥልቀት ፣ 12 የውኃ መጠን ፍተሻና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ፣ 3 የአናት ስራና የእጅ ፓምፕ ተከላ ፣ 5 የጉድጓድ ጠረጋ በጠቅላላው 30 ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ማጠናቀቅ  መቻሉን እና አፈፃፀሙ  65.98% መሆኑን መገምገም ተችሏል፡፡

  • የፋይናንሻል ዕቅድ አፈፃፀሙም  ፡-

በሩብ ዓመቱ በሁለቱም ዘርፎ ለታቀዱ ፕሮጀክቶች ብር 450,003,577.86 ወጪ በማድረግ ብር 516,658,327.69 ገቢ ስራ ለመስራት ታቅዶ ብር 368,861,574.19(81.97%) ወጪ በማድረግ ብር 385,867,444.07 (74.69%) ገቢ መገኘቱ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም  በኮርፖሬሽኑ የማምረቻ ማዕከል (manufacturing workshop)፡- የተለያዩ የፕሮጀክት ግብአቶችን በማምረት ፣ የሞደፊክና የብየዳ ስራዎችን በመስራት በሩብ ዓመቱ ብር1,100,000.00 የሚያወጣ ስራ ለመስራት ታቅዶ አፈፃፀሙ ብር 552,541.4(50.2%)  የተገኘ ሲሆን በኮርፖሬሽኑ  የኦፕሬተር ስልጠና ማዕከል   በደረቅ-2 ፣ በደረቅ-3 ፣ በኤክስካቫተር ፣ በሎደርና በትራክተር ኦፕሬተር ስልጠና በበጀት አመቱ ብር 2,552,816 ገቢ ለማስገባት ታቅዶ  በሩብ ዓመቱ   ብር 547,326.63  በመገኘቱ ከበጀት ዓመቱ 21.4% ገቢ  እንደተደረገ  መገምገም ተችሏል፡፡

  • የሃብት አጠቃቀም
    • የግንባታ ግብዓት አጠቃቀም

የፕሮጀክቶች የሩብ ዓመት የግንባታ ግብአት አጠቃቀም ሲገመገም ከጠቀመጠው ስታንዳርድ አንፃር ውስንነት ያለበት መሆኑን በስፋት የተስተዋለ ሲሆን በቀጣይ መስተካከል እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

  • የተሸከርካሪና ማሽነሪ አጠቃቀም

በዋናው ቢሮ ስር በሚገኙ ፕሮጀክቶች በጣም ከፍተኛ የሆነ የማሽነሪና ተሸከርካሪ አጠቃቀም ብክነት እንዳለ የሚያሳይ በመሆኑ ችግር ያለባቸውን ፕሮጀክቶች ለይቶ ፈጣን ማስተካከያ ማድረግ እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

  • የቴክኖሎጅ አጠቃቀምና ዲጅታላይዝ ከማድረግ አኳያ

 ሰው ሃብት አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ፣ የክፍያ ዝግጅትና ክትትል ሲስተም ሶፍትዌር ፣ የተቀናጀ የንብረትና ግዥ መረጃ አስተዳደር ሲስተም (ERP) ፣ የደህንነት ካሜራ (CCTV Camera) መግጠምና ወደ ስራ ማስገባት እና የፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም  በማልማት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

5. ጠንካራ ጎኖች፣ድክመቶች፣ያጋጠሙ ችግሮች እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

5.1.  ጥንካሬዎች

  1. የክረምት ስራዎችን በመለይትና በማቀድ እንዲሁም አፈፃፀማቸውን በየሳምንቱ በመገምገም ተግባራቱ በተያዘላቸው የድርጊት መርሃ-ግብር መሰረት እንዲጠናቀቁ በየደረጃው ርብርብ የተደረገ መሆኑ፣
  2. የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር ዕቅድ በጥንቃቄ በማዘጋጀት ሁሉም የስራ መሪ በተገኘበት የማስረጽ ስራ መሰራቱና የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ፤ 
  3. ለሁሉም ዘርፎችና ዳይሬክቶሬቶች፣ሜጋ ፕሮጀክቶችና ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እንደ ስራ ባህሪያቸው በዕቅዱ የተካተቱ ግቦችን፣መለኪያዎችንና ዒላማዎችን ግልጽና ሊለካ በሚችል አግባብ የወረደ መሆኑ፤
  4. የጸጥታ ችግሩ የሚፈጥራቸውን ውስብስብ ችግሮች በመቋቋምና የሚፈጠሩ ቀዳዳዎችን በመጠቀም ፕሮጀክቶችን ለማንቀሳቀስ የተደረገው ጥረትና የተገኘው ውጤት ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲጻጸር የተሻለና የሚያበረታታ መሆኑ፤
  5. ፕሮጀክት ተኮር የክትትልና ድጋፍ ስርዓት በመከተል የፕሮጀክቶችን የየዕለት እንቅስቃሴ መረጃ በመለዋወጥ እንዲሁም በየሳምንቱ በቋሚነት በዋና ስራ አስፈጻሚው ሰብሳቢነት የሚመለከታቸው በተገኙበት በመገምገም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቶሎ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት መደረጉ፤
  6. በጉድጓድ ቁፋሮ ዘርፍ ከክልሉ ውጪ በጉድጓድ ቁፋሮ ዘርፍ ከክልሉ ውጪ ስራዎችን በማፈላለግና በመሰማራት ውጤታማ ስራ መሰራቱ፤
  7. ክፍያዎችን በወቅቱ የመጠየቅ፣የማጸደቅና የመሰብሰብ አፈጻጸማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱና ለበርካታ አመታት ሲንከባለሉ የመጡ በርካታ የክፍያ ኬዞችን መቋጭት መቻሉ፤

5.2. ድክመቶች

  1. አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በተራዘመ ጊዜና ቁርጠኝት በሌሎች ቦታዎች በጸጥታ ችግሩ ምክንያት ያልሰናቸውን ስራዎች በሚያካክስ መልኩ በመስራት ላይ ክፍቶች መኖራቸው፤
  2. ፕሮጀክቶች ከተገባባቸዉ ዉል አኳያ የኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን እየሰራበት ያለዉን አጠቃላይ ሁኔታ የመከታተል እና የማስተካከል ክፍተቶቻችን የቀጠሉ መሆናቸው፤ 
  3. ካሰማራነው ወይም ካለን ሀብት አንጻር ውጤታማነታችን ዝቅተኛ መሆን፤
  4. የክረምት ስራዎችን በተቀመጠላቸው ጊዜ አሟጦ በመተግበር በኩል መንጠባጠቦችና መጓተቶች መታየታቸው፤
  5. የግዥ ግብአት አቅርቦት መጓተት የታየ መሆኑ፤
  6. የጥገና ድግግሞሽ መብዛት እና በብልሽት ምክንያት በርካታ ጊዜ መባከኑ፤
  7. 5.3.   ከአቅም በላይ የነበሩ ችግሮች
  8. የጸጥታ ችግሩና የጸጥታ ችግሩ በወለዳቸው በርካታ ውስብስብ ችግሮች ምክንያት ፕሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ ስራ ለማስጀመር አለመቻሉ ፣ ለተሰማራንባቸው ፕሮጀክቶችም የሚያስፈልጋቸውን ግብአት በወቅቱና በሚፈለገው መጠን ማድረስ አለመቻሉ
  9. በከፍተኛ መጠንና በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት ወጪአችን ያሳበጠ ከመሆኑም በላይ ውል ገብተን ለምንሰራቸው ስራዎች በአሰሪዎቻችን በኩል የተፈቀደልን የዋጋ ማሻሻያ ወጪውን በአግባቡ የማይሸፍን መሆኑ፤
  10. የሪግ መለዋወጫ ሀገር ውስጥ ገቢያ እንደልብ የማይገኝ በመሆኑ የጉድጓድ ቁፋሮ አፈጻጸም ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ፤  ስሚንቶ ፣ ነዳጅና የመሳሰሉት ቁልፍ ግብአቶች እጥረት፤
  11. በአማካሪና በአሰሪ ድርጅቶች በኩል የተንዛዛ የውሳኔ ሂደት በመኖሩ ክፍያ ለማጸደቅና ለመሰብሰብ እንቅፋት መሆኑ፤
  12. በፕሮጀክት ባለቤቶች በኩል የወሰን ማስከበርና የመደረሻ መንገዶች ችግሮችን ቀድሞ ባለመፍታት የተነሳ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጓተት፤
  13. በህውሀት ጦርነትና አሁን ላይ በተከሰተው የፀጥታ ችግር የተዘረፈና የወደመ ንብረት እንዲሰረዝ ለሚለከታቸው የቀረበ ቢሆንም አለመሰረዙ የኮርፖሬሽኑን ሀብት ያለአግባብ ያሳበጠ መሆኑ፤

5.3. ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

  1. ውስብስብ በሆነ ችግር ውስጥ እንደ መሆናችን ስራዎች ከእኛ በኩል በሚፈጠር ጉድለት  እንዳይጓተቱ በየጊዜው በየደረጃው እየገመገሙና እያስተካከሉ መሄድ፤
  2. የሰራተኛችን የስራ መነሳሳትና በችግር ውስጥ ሆኖ የመስራት ሞራሉን መጠበቅ፣መጠቀምና ማበረታታት፤
  3. የስራ መሪዎች በስራቸው ለተመደበው ሰራተኛ ስራውን ለመስራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት እንዲኖረው የስራ ላይ ስልጠና እንዲሰጡ በማድረግና መስጠጣቸውን በመከታተል መዋቅርና አደረጃጀቱን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ማስገባት
  4. ለዘርፉ፣ለዳይሬክቶሬቱ ወይም ለክፉሉ ከወረዱ ግቦች፣መለኪያዎችና ዒላማዎች ጋር የተሳሰረ ፣ግልጽና ሊለካ የሚችል የBsc እቅድ በማዘጋጀት ከሰራተኛው ጋር መፈራረም፤
  5. ክፍያዎችን በወቅቱ መጠየቅ ፣ ማፀደቅና መሰብሰብ ስራ በልዩ ትኩረት መስራት፤
  6. በክረምቱ ያልሰራናቸውንና የተጓተቱ ስራዎችን ለይቶ በቶሎ መፈጸም፤
  7. 7.  በግብአት አቅርቦት መጓተት፣በተሽከርካሪና ማሽነሪ ብልሽት እንዲሁም በእኛ አቅም ሊፈቱ በሚችሉ የይዞታ ፣ የመግቢያ መንገድ፣ሶስተኛ ወገን ችግሮች ምክንያት ፕሮጀክቶች እንዳይጓተቱ ርብርብ ማድረግ   በሚል የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም   በአሰሪዎች  ደረጃ መገምገም ተችሏል፡፡
  8. በመጨረሻም ኮርፖሬሽኑ  በሩብ  ዓመቱ በቢዝነስ ዴቭሎፕመነትና ኢኖቬሽን ዋና ዳይሬክቶሬት  በአይሲቲ የስራ ከፍል   ሶፍት ዌር ያለሙና ወደ ስራ እንዲገባ ላደረጉ  የስራ ክፍል ኃላፊና  የአይሲቲ ባለሙያዎች   ብር እና የምስክር ወረቀት የማባረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል ፡፡ ይህም ሌሎችን  ለስራ የሚያነሳሳ እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቷል
Scroll to Top